ከምርጫ ጋር በተያያዘ ህገመንግስቱ ራሱ ነባራዊ እውነታን ይጥሳል! Seyoum Teshome
በመጀመሪያ ደረጃ ከምርጫ ጋር በተያያዘ የህገመንግስት ጥሰት ተፈፅሟል የሚባለው ፍፁም ስህተት ነው። ከዚያ ይልቅ ህገመንግስቱ በራሱ ነባራዊ እውነታን ይጥሳል። ህወሓቶች "በራሳችን ምርጫ እናደርጋለን" ማለታቸው ደግሞ ህገመንግስቱን ይጥሳል። በአንድ በኩል ህገመንግስቱን እየጣሱ በሌላ በኩል ያልተጣሰውን ተጥሷል ይላሉ። "ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ያለቅሳል" የሚሉት አይነት ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ህወሓቶች ምርጫ የሚባል ነገር እንዲካሄድ አይፈልጉም። ከዚያ ይልቅ ከምርጫው ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ችግር እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ከህወሓት ጋር መታረቅ ነው። ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ህወሓት በፌደራል ደረጃ ስልጣን መጋራት የሚችልበት ሁኔታ የለም። በቀጣዩ ምርጫ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ህገመንግስቱ ራሱ ነባራዊ እውነታን ይጥሳል! እንደ ቀድሞ ማሸነፍ አይችልም። ቢያሸንፍ እንኳን ከክልል ወጥቶ ማስተዳደር አይችልም። በሁሉም የኢትዮጵያ ጥግ ሲፈነጩ የኖሩ ሰዎች አሁን መቀሌ ውስጥ ተወሽቆ መኖር ሰልችቷቸዋል። ስለዚህ "መቀሌ ላይ ምርጫው መካሄድ አለበት" እያሉ አዲስ አበባ ላይ ግን በተወካያቸው አቶ ልደቱ አያሌው በኩል ደግሞ "ከእርቅ በፊት ምርጫ መካሄድ የለበትም" እያሉ ነው። ምክንያት ሲባል ደግሞ "ብልፅግና እና ህወሓት ሳይታረቁ ምርጫ ቢካሄድ ሀገር ይበጠበጣል" ይላችኋል። ስለዚህ አሁን ላይ ብጥብጥ የሌለው ህወሓቶች አርፈው ስለተቀመጡ እንደሆነ እየነገረን ነው። ልደቱ የሚናገረው ደግሞ ህወሓቶች እንዲህ ብለህ ተናገር ብለው የነገሩትን ነው።
በእርግጥ ብልፅግና ፓርቲ ከህወሓት ጋር ለመታረቅ ፍቃደኛ ሳይሆን ከቀረ ግን እንደምንም አጭበርብረው "የራሳችንን ምርጫ አድርገናል" በማለት የክልሉ መስተዳድር ላይ ሙጭጭ ሊሉ ይችላሉ። ለማንኛውም አካሄዳቸውን በጥሞና ማጤን ተገቢ ነው።
- Category
- Ethiopian News