#Ethiopia #TPLF #Amhara #Tigray
ጥይት ጨርሶ በድንጋይ የጦር መሳሪያ የማረከው ጀግና
ጥይት ጨርሻለሁ ብዬ መሸሽ አልፈለኩም የሕወሓትን ታጣቂ በድንጋይ በመምታት ሙሉ ትጥቅ ማርኩኝ - የአንኮበር ሚሊሻ
ሚሊሻ አለሙ ላቀው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንኮበር ወረዳ የማህል ወንዝ ቀበሌ ነዋሪ ነው።
ወራሪውና ተስፋፊው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ሰርጎ በመግባት በሰውና በንብረት ላይ እያደረሰ ያለውን ውድመት በሰማሁ ጊዜ አራት የቤተሰብ አባላት ቢኖረኝም ግንባር ከመሄድ የሚያግደኝ ምንም ነገር የለም፤ ከሃገር አይበልጥምና በማለት ነው ወደ ግንባር ያቀናሁት ብሏል።
ሚሊሻ አለሙ ላቀው ጠላትን ለመፋለም ወደ ግንባር ባቀናበት ጊዜ ታጥቆት የነበረው የጦር መሳሪያ ኋላቀር ሲሆን በወቅቱ ከመከላከያ ጋር በመሆን ከጠላት ጋር ሲፋለም ጥይት ይጨርሳል።
እንደ ሚሊሻ አለሙ ላቀው ገለፃ "ጥይት ጨርሻለሁ ብዬ መሸሽ አልፈለኩም ይልቅ ጠላት በመማረክ ይህን ስግብግብ ቡድን ድል ሳላደርግ አልመለስም" የሚል ወኔን ተላብሸ ምሽግ ላይ እራሴን ለትንቅንቅ አዘጋጅቼ መጠበቅ ጀመርኩ ይላል።
ብዙም ሳይቆይ ጠላት ወደ ምሽግ ሲጠጋ ትንቅንቅ በማድረግ ጠላትን በድንጋይ በመምታት ከጣለው በኋላ የያዘውን መሳሪያ ነጥቆ በመደምሰስና ሙሉ ትጥቁን በመማረክ አኩሪ ጀብዱ ፈፅሟል።
አሁን ላይ "ከጠላት የማረኩትን መሳሪያና ሙሉ ትጥቅ በመያዝ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ይህን ጠላት እስኪቀበር እዋጋለሁ" ሲል ሚሊሻ አለሙ ላቀው ገልጿል።
የአካባቢዬ ህዝብ መሬቴን አያረሱልኝ ይገኛሉ ያለው ሚሊሻ አለሙ ላቀው የወረዳው የስራ ኃላፊዎችም ቤተሰቦቼን እንደሚደግፏቸው በመግለፅ አበረታተውኛል ማለቱን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
- Category
- Ethiopian News