#Ethiopia #Schools #Covid19ethiopia
-
DW Amharic : በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በኢትዮጵያ ላለፉት ሰባት ወራት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ዛሬ በከፊል ተጀምሯል። ዛሬ ሰኞ ጠዋት እንደተመለከትነው በቅርቡ ለሀገራዊ ፈተና የሚቀርቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ መደበኛ የትምህርት ገበታቸው የተመለሱ ሲሆን በሂደት ዩኒቨርሲቲዎች ጨምሮ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ወደ መማር ማስተማር ስራቸው እንደሚገቡ ተገልጿል። በመቐለ የሚገኘው ማጂክ ካርፔት የተባለ ትምህርት ቤት ለኮረና ቫይረስ ጥንቃቄ ሲባል በአንድ ክፍል 25 ተማሪዎች ብቻ በመያዝ መደበኛ ስራውን ሲከውን ተመልክተናል።
- Category
- Ethiopian News