Loading...

አስደማሚው ዐይነ ሥውር የፈረስ ጉግስ ተወዳዳሪ እና አሸናፊ በአዊ

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis
ዐይነ ሥውሩ የፈረስ ጉግስ ውድድር አሸናፊ!
(አብመድ) አስደማሚው ዐይነ ሥውር የፈረስ ጉግስ ተወዳዳሪ እና አሸናፊ

በአዊ ብሄረሰብ አሥተዳድር ፈረስን ለክብረ በዓላት ማድመቂያ እንዲሁም የተለያዩ ማኅበራዊ ክሥተቶችን ልዩ ገጽታ ለማጎናጸፍ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

በተለይም በበዓላት ጊዜ የሚከወነው የፈረስ ጉግስ ውድድር ቀልብን የሚስብ ትዕይንት ነው፡፡ የፈረስ ጉግስ እና ሽምጥ ውድድር ደግሞ ለዐይናማዎችም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ነው፤ ፉክክሩ የሚከወነው በከፍተኛ ፍጥነት መሆኑንም ልብ ይበሉ፡፡ ለዚህም ነው የዐይነ ሥውሩ ተወዳዳሪ ድርጊት የብዙዎችን ቀልብ የሳበው፡፡

በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አሥተዳድር ፋግታ ለኮማ ወረዳ የሚገኙት የአቶ አዲስ ሰውነት ተሰጥዖ እንግዳ እና ትኩረትን የሳበ ሆኗል፡፡ ባለተሰጥዖው አቶ አዲስ የዐይን ብርሃናቸውን ያጡት ከ8 ዓመታቸው ጀምሮ ነው፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ የ‹‹እችላለሁ›› ስሜት አላቸው፤ ይህንንም በተግባር እያሳዩ ነው፡፡

ለ80ኛ ዓመት የሰባት ቤት የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ክብረ በዓል ቅድመ ዝግጅት ላይ በተደረገ ውድድርም አሸናፊ ሆነዋል፡፡ እንዴት ይህንን ለማድረግ አሰቡ? እንዴትስ ማሳካት ቻሉ? ተብለው ሲጠየቁም ‹‹ሁሉንም ነገር ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አልልም፤ እወድቃለሁ ብዬም አልሰጋም›› ነው ያሉት ዐይነ ሥውሩ ፈረሰኛ፡፡

በብሔረሰብ አሥተዳድሩ የፊታችን ጥር 23/2012 ዓ.ም የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች 80ኛ ዓመት በዓል ይከበራል፡፡

በዓሉ በብሔረሰብ አሥተዳድር ደረጃ ወደ ሚከበርበት እንጅባራ ከተማ በማምራት ይህንን ልዩ ትዕይንት ቢታደሙ ደግሞ ዐይነ ሥውር፣ ነገር ግን ልበ ብርሃኑን የፈረስ ጉግስ ተወዳዳሪ መመልከት ይችላሉ፡፡

ለዐይናማዎች ፈታኝ እና ከፍተኛ ጥንቃቄ በሚጠይቀው፤ በከፍተኛ ፍጥነት በሚከናወነው የፈረስ ጉግስ ውድድር ዐይነ ሥውሩ ተወዳዳሪ ከፉክክር አልፎ ማሸነፋቸው ልዩ ትኩረትን ስቧል፡፡
Category
Ethiopian News

Post your comment