የህዳሴው ጎድብ ግንባታ ከተጀመረ በኋላ ግብፆች የአባይ ጉዳይ በሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ስር እንዲሆን አድርገዋል። የኢትዮጵያና ሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች ከግብፆች ጋር በሚያደርጉት ድርድር ውሳኔ የሚሰጠው የግብፅ ውሃ ሚኒስቴር ሳይሆን የግብፅ ደህንነት ሃላፊ ነው። ስለዚህ ግብፆች በአባይ ላይ የሚያደርጉት ድርድር የውሃ ጉዳይ መሆኑ ቀርቶ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ ከሆነ ሰንብቷል። የኢትዮጵያን የውሃ ሚኒስትር ከግብፅ የደህንነት ሃላፊ ጋር እንዲደራደር ማድረግ ተገቢ አይደለም። ከዚያ ይልቅ የአባይና የህዳሴውን ግድብ የተመለከቱ ስራዎችን የሚሰራ ብሔራዊ ኮሚቴ ሊቋቋም ይገባል። በተለይ በውሃና ኢነርጂ፣ በውጪ ጉዳይ እና በመረጃና ደህንነት መስሪያቤቶች ውስጥ በአባይ ድርድር ዙሪያ ላይ የሚሰሩ የሥራ ክፍሎች (ዴስኮች) ሊቋቋሙ ይገባል። እነዚህን የስራ ክፍሎች በበላይነት የሚመራ በሚኒስቴሮች ደረጃ ብሔራዊ ኮሚቴ መዋቀር አለበት።
***
- Category
- Ethiopian News