Loading...

አቶ ልደቱ አያለው - የፖለቲካ ተዋናይ ወይስ የህወሓት ተላላኪ?

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

አቶ ልደቱ አያለው ሰሞኑን ተነስቶበታል። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የፖለቲካ ነጥብ ለማግኘት ይታትራል። ነገር ግን ብዙዎች አቶ ልደቱን በከሃሊነት ስለፈረጁት የሚናገረውን ነገር ይሰሙታል እንጂ አያዳምጡትም። በመሆኑም ከንግግሩ በስተጀርባ ያለው ውጥን ሃሳብ ምን እንደሆነ በትክክል ማሰብና በግልፅ መለየት የቻሉ አይመስለኝም። በእርግጥ ከአቶ ልደቱ ሰሞንኛ ባህሪ በስተጀርባ ያለው ማን እንደሆነና በተገኘው ሚዲያ ላይ እየቀረበ አስር ነገር የሚናገረው ዝም ብሎ ትኩረት ከመሻት አሊያም የከሰመውን የፖለቲካ እድል መልሶ ለማንሰራራት ከመሰላችሁ ፍፁም ተሳስታችኋል። ልደቱ እያደረገ ያለው በጣም የታቀደበትና ካለፈው አመት መጋቢት 2011 ጀምሮ በእቅድ እየተሰራ ያለ ፖሮጀክት ነው። ምርጫው ከተካሄደ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች፣ ወደ ቅድመ 2010 ትመለሳለች፣ ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ ለማድረግ በስነ-ልቦና ዝግጁ አይደለም፣... ወዘተ የሚለውን ደግሞ ደጋግሞ የሚናገረው ስለ ምርጫ፣ ህዝብ፣ ሀገርና መንግስት አይደለም። ይህን ሚስጥር ለማወቅ የሚያስችለውን ፍንጭ ያገኘሁት ከአቶ ልደቱ አያሌው ጋር ለመጀመሪያ ግዜ በአካል የተገናኘን እለት ነው። ባለፈው አመት በአንድ የውይይት መድረክ ላይ ለመሳተፍ በቀጠሮው መሠረት አዲስ አበባ ካዛንቺስ በሚገኘው ራዲሰን ብሉ ሆቴል ስደርስ የውይይቱ መሪ አቶ ልደቱ ሆኖ አገኘሁት። በአዳራሹ ውስጥ ከነበሩት ሰዎች ውስጥ በግምት ከ90% ባላይ የሚሆኑት የትግራይ ተወላጆች ናቸው። አለ የተባለ የትግራይ ምሁር፣ አክቲቪስት፣ ፖለቲከኛ፣ ጋዜጠኛ፣... የሃይማኖት አባት አልቀረም፣ ሁሉም በአዳራሹ ተገኝተዋል። የትግራይ ተወላጅ ያልሆኑት ቀንደኛ የህወሓት ተላላኪ የሆኑት የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) አባላት፣ ኦቦ በቀለ ገርባ፣ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ እንዲሁም በእኔ ጋባዥነት በዝግጅቱ ላይ የተገኙት አምስት ጓደኞቼ ናቸው። የውይይት መድረኩ ሙሉ በሙሉ እኔን "Abuse" በማድረግ ክፉ ለማናገር ያለመ ነው ማለት ይቻላል። አዳራሹ ውስጥ ፎቶ ማንሳት ሆነ ቪዲዮ መቅረፅ እንደማይቻል ተነጋግረን የነበረ ሲሆን ከመድረኩ አጠገብ የተቀመጠው ዳዊት ከበደ በድብቅ ድምፃችንን እየቀረፀ ነበር። በማግስቱ በእኔ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት፣ ስድብና ማንጓጠጥ ለብቻው ኢዲት በማድረግ Awramba Times ላይ አወጣው። ከዚያን ቀን በኋላ የሁለት ሰዎችን እንቅስቃሴ እና ንግግር በጥሞና መከታተል ጀመርኩኝ፦ የመድረኩ መሪ የነበረው ልደቱ አያሌው እና የዋና አዘጋጁ ዩሃንስ መዝገበ። የሁለተኛውን ሰውዬ ሥራና እንቅስቃሴ አስመልክቶ ከሁለት ወር በፊት "ስብሃት ነጋ በአዲስ አበባ" በሚል ርዕስ እዚሁ ቻናል ላይ አውጥቼዋለሁ። እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ የአቶ ልደቱ ሃሳብና እንቅስቃሴ አልያዝ፥ አልጨበጥ ብሎኝ ነበር። ይሁን እንጂ ሰሞኑን ከሚያደርገውና ከሚናገረው ዓለማና ግቡ ምን እንደሆነ መገመት ይቻላል። በዚህ መሠረት ልደቱ ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ሌላ ትልቅ ፕሮጀክት ይዞ እንደመጣ እርግጠኛ መሆን ይቻላል። በዚህ ፕሮግራም የልደቱን ንግግርና እንቅስቃሴ ከፖለቲካ ቲያትር አንፃር በዝርዝር እንዳስሳለን። በመጨረሻም ሰውዬው ከህወሓቶች ጋር በመሆን የወጠነውን እቅድና ተንኮል አንድ በአንድ እየነቀስን እናወጣለን።
***
Attribution:
Background Music፦ Wushetam || ውሸታም - Official Music Video by Zeritu Kebede is Published on 20 Apr 2017. The music video is licensed under a Creative Commons Attribution licence (https://creativecommons.org/licenses/by/4.0/)

Source: https://youtu.be/h7OtD5uWXrY

Artist (Youtube Channel): https://m.youtube.com/channel/UCvjLlsveJkYOHKzkTmhkQaw/about

Category
Ethiopian News

Post your comment