Loading...

ይሄ በሽታ ይመለሳል። መድኃኒቱ ይገኛል። ኢንሻህ አላህ ! - ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

ይሄ በሽታ ይመለሳል። መድኃኒቱ ይገኛል። ኢንሻህ አላህ!
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ
ይህን የሚያህል አይደለም። አንቀጥቅጦታል፤ እንዲህ ትንሽ ተንቀጥቅጧል። ትንሹም ትልቁም፣ ሀብታሙም ደሀውም። ታላቅ ነኝ፣ ከእኔ በላይ የለም የሚለው ሁላ ተንቀጥቅጧል። ስለተንቀጠቀጠ በሽታው መፈወሱ መመለሱ አይቀርም። መድኃኒቱ መገኘቱ አይቀርም።
ግን እኛ ካልተመለስን፣ ሌላ ደግሞ በሽታ ይመጣል። ሌላ ደግሞ ከዚህ የባሰ ይመጣል፤ አንቀጥቃጭ ይመጣል። አንዴ ሙልጭ አድርጎ የሚያጠፋ ይመጣል። ከሞት በኋላም እኮ አደጋ አለ። መቃብርም እኮ አደጋ አለ። በዓለም ብቻ አይደለም።
እና አገራችንን አላህ ሰላም ያድርግልን። ሁላችንም በእውነት የምንመለስ አላህ ያድርገን። ልባዊ መመለስ የምንመለስ አላህ ያድርገን። አላህን የምንሰማ አላህ ያርገን። ፈጣሪ ጌታ ያየናል ይሰማናል የምንል አላህ ያድርገን።
በቤተክርስቲያን እየገባን፣ በመስኪድ እየገባን ችግር እየፈጠርን ነው እኮ ያዘጋነው። መስኪድ ተዘግቶ ያውቃል? ቤተክርስቲያን ተዘግቶ ያውቃል?
እዚያ ውስጥ የምንሰራውን ያውቃል እሱ። ስለሚያውቅ፣ "እናንተ የእኔ ባሮች አይደላችሁም፣ ጠላቶቼ ናችሁ ከቤቴ ውጡ" ብሎ በአጠቃላይ አወጣን። ከዚህ ወዲያ ምን ይሰራል አላህ? ብናሞኘው ይሞኛል?
አላህ አገራችንን በሰላም ይሸልምልን። ከልባችን የምንመለስ አላህ ያድርገን። - ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ

Category
Ethiopian News

Post your comment