Loading...

ህወሓት ቀድሞ የነበረውን የበላይነት ለማስመለስ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጦርነት ከፍቷል - ቲቦር ናዥ

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

TPLF using Violence to Restore its Lost Hegemony Says US Diplomat

የቀድሞ የበላይነቱን ለመመለስ ጦርነት የከፈተው ህወሓት
ህወሓት ከዚህ ቀደም በአገሪቱ የነበረውን የበላይነት ለማስመለስ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጦርነት ማድረጉን ቲቦር ናዥ ገለፁ፡፡
የህወሓት አመራሮች ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን ከስልጣን በማንሳት ላለፉት ዓመታት የነበራቸውን የበላይነት ለመመለስ ፍላጎት እንደነበራቸው የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ቲቦር ናዥ ለቢቢሲ ራዲዮ ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ የጦርነቱ ወታደራዊ ምዕራፍ ተጠናቆ የሰብኣዊ ምዕራፍ ላይ ይገኛል ያሉት ረዳት ሚኒስትሩ፤ የሲቪል ዜጎች ደህንነትን ለመጠበቅ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ሰብኣዊ ድጋፍን ለማቅረብ በኢትዮጵያ መንግስት እና በተባበሩት መንግሥታት መካከል የተፈረመው ስምምነት በአግባቡ ገቢራዊ እንዲሆንም ጠይቀዋል፡፡
በዚህ ረገድ በትግራይ ክልል ያለውን ጠቅላላ ሁኔታ ለማወቅ የመገናኛ አገልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ ሊመለሱ እንደሚገባም ቲቦር ናዥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያን ፖለቲካ እ.አ.አ. ከ1984 ጀምሮ ስከታተል ቆይቻለው ያሉት ረዳት ሚንስትሩ፤ ከህወሓት ጋር ያለው ችግር በአፋጣኝ ካልተፈታ ወደ ዘላቂ የሰርጎ ገብ አመፅ ሊያድግ እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

Tibor Nagy, US Ass. Sec for Africa made his stance clear again saying TPLF waged war on Ethiopia to restore its lost power. Amb. Nagy spoke to the BBC

Category
Ethiopian News

Post your comment