Loading...

አምስት የቤተሰባቸውን አባላት በአሸባሪው የህወሃት ያጡት አባት

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis
#FBC, #fana_news, #ፋና_ዜና

ነሐሴ 13 በደብረታቦር ከተማ አሸባሪው የህውሃት ቡድን በማለዳ አንድ የከባድ መሳሪያ የተኮሰ ሲሆን ምንም ጉዳት ሳያደርስ ነበር ያለፈው ፤ እሄ ስሜት በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ አንዳች አይነት ጥርጣሬን ያጫረ ቢሆንም ሁሉም ግነ የእለት ተእለት ስራውን አላቋረጠም ነበር ፤ እኩለ ቀን ላይ ግን በተከታታይ አምስት ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት አድርሷል፡፡

ዕለቱ የደብረታቦር በአል የሚከበርበት ህዘበ ክርስቲያኑ ወደ ቤተክርስቲያን ሄዶ የሚያስቀድስበት ስለነበር እሄንን ታሳቢ ያደረገ ይመስል ነበር የከባድ መሳሪያው ተኩስ ይላሉ የአካበባው ነዋሪዎች ፤ ሆኖም ያሰበው ባይሆንመ በቤተክርስቲያን አቅራቢያ ባሉ ቤቶች ላይ መሳሪያው አርፏል ፤ በዚህም 5 የቤተሰብ አባላት በቤታቸው ህይወታቸው አልፏል ፤ ሌሎች ሰዎችም አልፈዋል የአካል ጉዳትም አጋጥሟቸዋል ፤ ቤቶችም ወድመዋል ::

5 የቤተሰባቸውን አባል ያጡት አባወራን እና ቤተሰቦች በስፍራው የሚገኙ ባልደረቦቻችን አነጋግረዋቸዋል:: ስለሁኔታው ያሉትን መታገስ አየልኝ እንደሚከተለው አዘጋጅታዋለች።
Category
Ethiopian News

Post your comment