Loading...

ያለምንም ተኩስ ወደ ከተማዋ ገብተዋል - በህወሓት ተዋጊዎች መያዟን የአማራ ክልል መንግስት አረጋገጠ - ዶይቼ ቬለ

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

#TPLF #Lalibela #Ethiopia #Tigray #DW
አንድ የላሊበላ ከተማ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት የህወሓት ኃይሎች ትናንት እኩለ ቀን አካባቢ ያለምንም ተኩስ ወደ ከተማዋ ገብተዋል።በህወሓት ጥቃት ሊደርስብን ይችላል ብለው የሰጉ ከተማዋን ለቅቀው መውጣታቸውንም ነግረውናል።የአማራ ክልል መንግስት በየግንባሩ እየተመታ ያለው ህወሓት ላሊበላን እንደመውጫ መንገድ እጠቀማለሁ ብሎ ገብቷል ብለዋል

የህወሓት ተዋጊዎች ላሊበላ ከተማ መግባታቸውን የአማራ ክልል አረጋገጠ። የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ፣በየግንባሩ እየተመታ ነው ያሉት ህወሓት እንደ መውጫ መንገድ ሊጠቀምባት ላሊበላ ገብቷል ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።የዓይን እማኞችም ህወሓት ላሊበላን መቆጣጠሩን ገልጸዋል።በህወሓት ሊፈለጉ ይችላሉ የተባሉ ሰዎች ከከተማዋ እየወጡ እንደሆነም እየተነገረ ነው።ትናንት ላሊበላን የያዘው ህወሓት በየግንባሩ እየተመታ ነው ሲል የአማራ ክልል መንግሥት ለዶቼቬለ አስታውቋል።
አንድ የላሊበላ ከተማ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት የህወሓት ኃይሎች ትናንት እኩለ ቀን አካባቢ ያለምንም ተኩስ ወደ ከተማዋ ገብተዋል፣በህወሓት ጥቃት ሊደርስብን ይችላል ብለው የሰጉ ሰዎች ከተማዋን ለቅቀው መውጣታቸውንም ነግረውናል።የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ስለ ጉዳዩ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ህወሓት በየግንባሩ እየተመታ ስለሆነ ላሊበላን እንደመውጫ መንገድ እጠቀማለሁ ብሎ ገብቷል፣ ግን በቅርቡ እንስወግዳቸዋለን ብለዋል።የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ትናንት ማምሻውን “ያለመስዋዕትነት ድል አይታሰብም” በሚል ባወጣው መግለጫ ታሪካዊ ከተሞቻችንም ሆነ አጠቃላይ የአማራን ግዛት ከጠላት ወረራ መመከት የሚቻለው በጽናት በመታገል ነው ብሏል።መግለጫው አክሎም በማዕበል የሚዝል ክንድ እንደሌለን የሰሜን ወሎ ተራሮች ዘላለማዊ የታሪክ ምስክር እናደርጋቸዋለንሲልም ዝቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ጉብኝት ደረጉትና የአማራ ልዩ ኃይል ከትግራይ እንዲወጣ ፍላጎት ባሳዩት የአሜሪካ የተራድኦ ድረጅት የበላይ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር አስተያየትን አስመልክቶ ዋና ዳሬክተሩ ግዛቸው ሙሉነህ ሀሳቡ የማይተገበርና ያለቀለት ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል።የአማራ ዴሞክራቲክ ኃይል ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ በበኩላቸው የአማራ ኃይሎች በራሳቸው መሬት ላይ ነው ያሉ ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
አሜሪካውያንና አንዳንድ የአውሮጳ መንግስታት የእርዳታ መተላለፊያ መንገድ በወልቃይት በኩል እንዲከፈት ግፊት ማድረጋቸው ትርጉሙ ሌላ መሆኑን ያመለከቱት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ መምህር ቻላቸው ታረቀኝ ሲሆኑ መንግስት ያን ከፈቀደ በራሱ ላይ ሞትን መፍረድ ነው ብለዋል፡፡

Category
Ethiopian News

Post your comment