የዛሬ እንግዳችን በስክሪን ላይ ፊቱን ለማሳየት ብዙም ፈቃደኛ ያልሆነ፤ ነገር ግን ከስክሪን ጀርባ ደግሞ ብዙ ስራዎችን የሚሰራ ሰው ነው፡፡ በዋናነት የሚታወቀው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ በሚያቀርባቸው የዲስኩርና የሥነ ጽሑፍ ምሽቶችን በማቅረብ ነው፡፡ እንግዳችን በአሁኑ ሰዓት በፎክሎር ትምህርት የፒኤችዲ ዕጩ ተመራቂ ነው፡፡
በተጨማሪም በሆቴልና ቱሪዝም ሙያ በዲግሪ፣ በማስተር ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በነገረ መለኮት በዲግሪ እየተማረ ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ይመረቃል፡፡ እንግዳችን በዲቁና ክህነት ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ ይገኛል፡፡
ተወልዶ ያደገው በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ሰፈር ነው፡፡ የዲስኩር ምሽቶችን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ማቅረብ የጀመረው ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡ በዲስኩር ምሽቱ ላይ በርካታ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ እየሰራ ይገኛል፡፡
የአንድ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆነው ምስክር ጌታነው በተጨማሪም በብስራት ኤፍ ኤም ላይ የአሻም ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ነው፡፡
ባለትዳርና የ2 ልጆች አባት የሆነው ምስክር ጌታነው በበጎ አድራጎት ስራዎችም ንቁ ተሳታፊ ነው፡፡

- Category
- Ethiopian News