Loading...

የኢትዮጵያ ጦርነትና መዉጪያዉ ዘዴ - «ሐይ» ባይ ሽማግሌ እንዴት ጠፋ?

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

#Ethiopia #Tigray #DW

ለነፃነት የመስዋት ጀግንነትን ከመነጋገር ብልሐት፣ የመንግስታዊ አስተዳደር ሥርዓትን፣ ከሽምግልና ወግ የቀየጠ ባሕል አዳብራለች የምትባለዉ ኢትዮጵያ ዛሬ ዜጎችዋን የሚያረግፍ፤የሚያሰድድ፣ ለተመፅዋችነት የዳረገ ጦርነትን ማስወገድ አልቻለችም።
ጦርነቱ ምንም ምክንያት ቢሰጠዉ የርስ-በርስ መሆኑ ሊያከራክር አይገባም።እርግጥ ነዉ የርስ በርሱ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት የመቀሌና የአዲስ አበባ ፖለቲከኞችን ለመሸምገል የሞከሩ ነበሩ።ዉጊያዉ ከተጀመረ በኋላ ግን ተፋላሚዎችን ለማደራደር ወይም ለመሸምገል የሞከረ አንድም የሐገር ሽማግሌ፣ አንድም፣ የየትኛዉም የኃይማኖት አባት የለም።ካለም አልተሰማም።ከሁለት ሳምንት በፊት «ጉዳዩ የሚያሳስበን ኢትዮጵያዉያን» ያሉ ወገኖች ተፋላሚዎች ተኩስ አቁመዉ እንዲደራደሩ የሚጠይቅ ሰነድ አሰራጭተዉ ነበር።የሰነዱ አዘጋጆች እራሳቸዉ እንዳሉት ስማቸዉን እንኳን በይፋ ለመናገር አልደፈሩም።

Category
Ethiopian News

Post your comment