Loading...

ሱዳን ወዳጆቻችን በስጦታ በሰጡኝ ቴምር እሱን እየበላን 3 ቀን ያለማቋረጥ ተዋግተናል - ጀግናው ብ/ጀኔራል ሙሉዓለም አድማሱ

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

የጀግናው ብ/ጀኔራል ሙሉዓለም አድማሱ ተጋድሎ በራስ አንደበት
---
ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት አካባቢ በዳንሻ ከተማ ያልተጠበቀ፣ አሳዛኝ፣ አስደጋጭ ድርጊት ነው የተፈጸመው፡፡ የትህነግ ወራሪ ሀይል የቶክሰ እሩምታ በ5ኛ ክ/ር ጦር ካምፕ ላይ ከፈቱበት::
የክፍለ ጦሩን አዛዥ ብ/ጀ ሙሉዓለም አድማሱና ጦሩን ወራሪ ሀይል ከበባቸው:: እጅህን ሰጥ ተባለ እሱም "ደሜን ትጠጣታለህ እንጅ እጄን አትጨብጣትም" ብሎ መለሰላቸው::
ከምግቡ ይልቅ አሳሳቢ የነበረው ጥይት ነው ብለዋል፡፡
እነሱ እንደፈለጉት ነበር የሚተኩሱት ሲሉ ነግረውናል፡፡
አርቢጂ ተኮሱ ዲሽቃ ተኮሱ ብሬን ተኮሱ ቦንብ ወረወሩ እኛም ያለን አማራጭ ሰራዊቱ ወዲያውኑ ወደ ምሽጉ ገብቶ ራሱ ወደመከላከል አንዲገባ ማድረግ ነበር ሲሉ የወሰዱትን አማራጭ አጋርተውናል፡፡
ሦስት ቀን ሙሉ ያለ በቂ እህል ውሃ እንደተከበበ በ3ኛው ቀን ጀግናው መከላከያ ሰራዊት፣የአማራ ልዬ ኃይላችንና የአካባቢው ሚኒሻ ወራሪውን ጦር በመደምሰስ ጀግናውን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ብ/ጀ ሙሉዓለም አድማሱና ሙሉ ጦሩን ከከበባ በማውጣት ክሃዲዎችን በመቅበር በኢትዮጵያዊን ትብብር ድል ተቀናጅተናል ።
ያልተነገሩ ታሪኮችም በዛሬው ቃለመጠይቅ ተካተዋል፡፡
ይከታተሉ፡፡
አማራ ራዲዮን
amharaweb.com በቀጥታ መከታተል ይችላሉ

Category
Ethiopian News

Post your comment