ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምእራፍ - ዶ/ር ደብረጺዮንን ጨምሮ አራት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ተምቤን አቢ አዲ እንዲሁም የሀውዜንና አድዋ መገንጠያ በሆነችው “ወርቃምባ” ከተባለች ከተማ ይገኛሉ
የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ጸሐዬና ጌታቸው ረዳ በአንድ ቦታ ለይ መሆናቸውን በሰሜን ዕዝ የ31 ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ሻምበል በየነ አስታወቁ፡፡ ከአራቱ ውጭ ያሉ ሌሎች አመራሮች ደግሞ አዋሳኝ በሆኑ የአማራ ክልል የተከዜ ጫፍ ስፍራዎች በዋናነትም ልዩ ስሙ “አቅመራ” በሚባል ስፍራ ሲመላለሱ መታየታቸውን ገልጸዋል፡፡- በልዩ ጥበቃ ማለትም በኮማንዶ ጭምር እተየተጠበቁ እንደሆነ የተናገሩት አዛዡ ከአራቱ ባለስልጣናት ውጭ ሌሎች ብዙም በሕዝብ የማይታወቁ ባለስልጣናት በስፍራው እንዳሉ ስለማየታቸው ተናግረዋል፡፡እነርሱን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ በአጭር ቀናት ይጠናቀቃል፡፡
- Category
- Ethiopian News