Loading...

ኦነግ ሸኔ በአንድ ቀን 40 የፌዴራል ፖሊስ ነው የገደለው፤ እኛ ሸሽተን ነው የመጣነው።- አዲስ አበባ እስጢፋኖስ ቤ/ክ የተጠለሉ የወለጋ ተፈናቃዮች

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

በሽብርተኝነት የተፈረጀው ኦነግ ሸኔ በምሥራቅ ወለጋ ዞን የሚያደርሰውን ጥቃት የሸሹ 30 ሕፃናትን ጨምሮ 107 የአካባቢው ነዋሪዎች ከሦስት ቀናት በፊት አዲስ አበባ ገብተው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለዋል።ተፈናቃዮቹ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ፊት ለፊት በሚገኘው እስጢፋኖስ ቤተ ክርስትያን ነው ተጠልለው የሚገኙት።እነዚሁ ሰዎች እንደሚሉት ይኖሩበት በነበረው አካባቢ በሸኔ ታጣቂዎች ሰዎች ይገደላሉ፣ ይደፈራሉ ፣ ንብረተታቸው እንዲወድም እንዲወድም ይደረጋል።
ችግራቸውን ለወረዳም ሆነ ለዞን አቤት ቢሉም መፍትሔ ማግኘት እንዳልቻሉ እና ይህንን አዲስ አበባ አቤት ለማለት መምጣታቸውን ተናግረዋል። የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ችግሩ በተፈጠረበት አካባቢ የመንግሥት የፀጥታ አካላትንም እየገደሉ እንደሆነ እና ከቤት ንብረታቸው ነቅለው ለመውጣት ይህ ዕውነት እንደገፋቸውም ገልፀዋል።ካነጋገርናቸው ተፈናቃዮች መካከል የተወሰኑት ሸሽተው ሲወጡ ልጆቻቸው እና ባለቤቶቻቸው ተበታትነው በየጫካው ስለቀሩ የት እንደሚገኙ እንደማያውቁም ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
ቪድዮ፦ሰሎሞን ሙጬ

Category
Ethiopian News

Post your comment