Loading...

ግብፅ ሁለተኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ ሙሌት ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ለመጋፈጥ ዝግጁ ነች - የግብፅ መስኖ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢንጂነር ሞሐመድ ጋኔም

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

   مداخلة المتحدث الرسمي باسم وزارة الري المصرية

የግብፅ መስኖ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢንጂነር ሞሐመድ ጋኔም ሰኞ አመሻሽ ላይ ለ “አል-አረቢያ” ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ፡ ግብፅ ሁለተኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ ሙሌት ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ለመጋፈጥ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡ ቃል አቀባዩ የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ተጽዕኖ ለመቀነስ በመስኖ መስክ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ወደ ትግበራ መግባታቸውን አንስተዋል፡፡ “ይሁን እና በዓባይ ውሃ ላይ ያለንን ታሪካዊ መብት እንዳልተውን እናረጋግጣለን” በማለት በውሃ ክፍፍል ረገድ ግብፅ ያላት አቋም የጸና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አክለውም “በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ የሁሉም ወገኖች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የምንጥር በመሆኑ ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ የተወሰነ የአቋም ለውጥ ማሳየት አለባት” ብለዋል፡፡ “መረጃ ከመለዋወጥ በፊት በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ እንፈልጋለን” ሲሉም ነው ኢንጂነር ሞሐመድ የሀገራቸውን አቋም የገለጹት፡፡

Category
Ethiopian News

Post your comment