Loading...

አሜሪካ በኅዳሴ ግድብ ድርድር ሚዛናዊ አቋም ይዛ ብትቀርብ ኢትዮጵያ ወደ ድርድሩ ልትመለስ ትችላለች ብዬ አስባለሁ - የኔቫዳ ኮንግረስ አባል ስቴቨን ሐርስፎርድ

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

"አሜሪካ ሚዛናዊ አቋም ይዛ ብትቀርብ ኢትዮጵያ ወደ ድርድሩ ልትመለስ ትችላለች ብዬ አስባለሁ ሲሉ" የኔቫዳ ኮንግረስ አባል ስቴቨን ሐርስፎርድ ለአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስትር ስቴቨን ምኑችን ተናገሩ።

በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ሁሉም ወገኖች መደመጣቸውን፣ አሜሪካም ወገንተኛ አለመሆኗን ለማረጋገጥ ምን እያደረጋችሁ ነው ተብለው የተጠየቁት የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስትር ሴክሬታሪ ስቴቨን ምኑችን ጥያቄውን በቀጥታ ሳይመልሱ ቀርተዋል።

የኔቫዳ ኮንግረስ አባል ስቴቨን ሐርስፎርድ በበኩላቸው ሴክሪታሪውን በመሃል ጣልቃ እየገቡ ጉዳዩን በቀጥታ እንዲመልሱና የእርሳቸው ሚና ምን እንደነበር ጠይቀዋቸዋል።

ስቴቨን ምኑችን በበኩላቸው ከግብጽ በተጨማሪ ሱዳን ከስምምነት ሳይደረስ ግድቡ በውኃ ሊሞላ አይገባም የሚል አቋም እንዳላት በአሜሪካ ኮንግረስ Ways and Means Committee ለተባለ ኮሚቴ ተናግረዋል። ኮሚቴው ከውጭ ግንኙነት ጋር የማይቀራረብ የመንግሥት በጀት ላይ አተኩሮ የሚሰራ ነው።

የኔቫዳው የኮንግረስ አባል ስቴቨን ሖርስፎርድ ሚዛናዊ ብትሆኑ ኢትዮጵያ ወደ ድርድሩ ልትመለስ ትችላለች ብዬ አስባለሁ ሲሉ ለምኑችን ነግረዋቸዋል።

Category
Ethiopian News

Post your comment