ዝናቡ መጥቷል፣ በአባይ_ግድብ ላይ ቀውስ አጥልቷል‼
ለረጅም ግዜ ለተለያዩ ዓለምአቀፍ ሚዲያዎች በጋዜጠኝነት የሰራውንና አሁን ላይ የአለምአቀፉ የቀውስ ቡድን (International Crisis Group) ባልደረባ የሆነው William Davison ከባልደረባው #Alan_Boswell ጋር በመሆን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ጥልቅ የሆነ ትንታኔ ሰጥቷል። የሦስቱ ተደራዳሪዎች መሰረታዊ ልዩነት እና ፍላጎት፣ የአሜሪካ መንግስት፣ የአውሮፓ ህብረትን እና የአፍሪካ ህብረት (አገራት) በጉዳዩ ዙሪያ ያላቸውን አቋምና ሚና በዝርዝር አስረድቷል። የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን መንግስት በየፊናቸው የገጠሟቸው ችግሮች፣ ያለባቸው የፖለቲካ ጫና እና ውጥረት፣ የሌሎች ሀገራት ጣልቃ-ገብነትና ግፊት፣ ድርድሩ በአለምአቀፍ ደረጃ እና በሀገር ውስጥ የፖለቲካ ሃይሎች ዘንድ የሚኖረው ተፅዕኖ፣ የድርድሩ ቀጣይነትና የትኛው ወገን ስኬታማ ሊሆን እንደሚችል ገራሚ የሆነ ትንታኔ ሰጥቷል። ትንታኔው በተጨባጭ ማስረጃ፣ የረጅም ግዜ ልምድ፣ እንዲሁም በአዳዲስና አስገራሚ መረጃዎች የታጨቀ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ዊሊያም ለረጅም ግዜ በኢትዮጵያ የኖረና የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተል የውጪ ሀገር ጋዜጠኛ እንደመሆኑ መጠን ነገሩን የሚመለከተው ከሀገራዊ ስሜትና ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ ነው። በመሆኑም በዚህ ትንታኔ ላይ የቀረበው ሃሳብና አመለካከት አብዛኞቻችን ከምናውቀው እና እስከዛሬ ከሰማነው ፍፁም የተለየ ሲሆን ገለልተኛ የሆኑ የውጪ ሀገራት በህዴሴው ግድብ ዙሪያ የተፈጠረውን አለመግባባት እንዴት እንደሚያዩት በግልፅ ይጠቁማል። #GERD_Podcast በሚል የቀረበው ትንታኔ፦ "ዝናቡ መጥቷል፣ በአባይ ግድብ ላይ ቀውስ አጥልቷል" (As Rains Begin, Crisis Looms over the Nile Dam!) የሚል ርዕስ የቀረበው ትንታኔ በቅድሚያ https://Podcast.ausha.co/the-horn የቀረበ ሲሆን ለፌስቡክ እና ዩቲዩብ ተጠቃሚዎች ማድረስ ይቻል ዘንድ እንደሚከተለው ቀርቧል።
- Category
- Ethiopian News