የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሉክዘመበርግ ያካሄዱትን የ1 ቀን ስብሰባ አመሻሹን አጠናቀዋል። ስብሰባው በ3 ጉዳዮች ላይ ሲመክር ውሏል።
ከስብሰባው አጀንዳዎች አንዱ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ ላይ ስለሚጣል ማዕቀብ ለመነጋገር የተሰበሰበው የዛሬው የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክክር በጉዳዩ ላይ ሳይስማማ ተለያይቷል።
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የህብረቱ አባል አገራት በኢትዮጵያ ጉዳይ ከበድ ያለ እርምጃ ለመሰድ በማመንታታቸው ስብሰባው ያለስምምነት ተጠናቋል።
- Category
- Ethiopian News