Loading...

እርምጃ ውሰዱ ስላልተባልን ከሞት ልናስጥላችሁ አንችልም፣ ከቻላችሁ ራሳችሁን ጠብቁ - በወለጋ የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች

Thanks! Share it with your friends!

You disliked this video. Thanks for the feedback!

Added by addis

“ዘር ተኮር የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፅሞብናል” ሲሉ በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ከጥቃቱ የተረፉ አማራዎች

ትናንት ምሽት በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ቦኔ ቀበሌ በንጹሐን አማራዎች ላይ የጀምላ ጭፍጨፋ መፈፀሙን ከጥቃት የተረፉ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ትናንት ምሽት 1 ስዓት አካባቢ የታጠቁ የኦነግ ሸኔ አባላት ወደ ነዋሪዎቹ ቀየ ዘልቀው በመግባት ንጹሐን አማራዎች ላይ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል ነው ያሉት፡፡
ነዋሪዎቹ ከዚህ ቀድሞ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ሲዛትባቸው እንደነበር ገልፀው ትናንት ምሽት “ዘር ተኮር የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፅሞብናል” ብለዋል፡፡
ከምሽቱ 4 ስዓት ጀምሮ የጸጥታ ኃይል በአካባቢው ቢደርስም እርምጃ እንድንወስድ ስላልታዘዝን ራሳችሁን ጠብቁ በሚል ብቻ መመለሳቸውን ነግረውናል፡፡
አሁንም ተደጋጋሚ ግድያ ላለመፈፀሙ ምንም ዋስትና የለንም ያሉት ከጥቃት የተረፉ አስተያየት ሰጭዎቹ መንግሥት በአፋጣኝ ደርሶ እንዲታደጋቸው ጠይቀዋል፡፡
የኦሮምያ ክልል መንግሥት በአካባቢው በኦነግ ሽኔ ግድያ መፈጸሙን ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል፤ ጉዳዩን አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡን በተደጋጋሚ የደወልንላቸው የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እና ምክትል ኮሚሽነር ስልካቸውን ሊያነሱልን አልቻሉም፡፡
Category
Ethiopian News

Post your comment