ከወሰን ውጪ አልፈዋል፤ መንገድ ዘግተዋል በተባሉ በየመንደሩ በሚገኙ ሱቆችና መደብሮች ላይ ሰሞኑን እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ተመልክተናል፡፡
እንዲሁም በጎዳና ላይ በህገ-ወጥ መንገድ እየሰሩ ነው በሚል በከተማዋ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት የሚታየው ማሳደድና ሩጫ ተበራክቷል፡፡
ፅ/ቤቱ እየወሰደ ያለው እርምጃ እኛ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ነው ተደራጅተን እንድንሰራ ይፈቀድልን ስንል የሚሰማን አጣን በሚል በጎዳና ንግድ ላይ የተሰማሩ ወገኖች ቅሬታ ያቀርባሉ፡፡
- Category
- Ethiopian News