የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ ጃኮብሰን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን መገናኘታቸው ተሰምቷል። በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መወያየታቸው ታውቋል። ሰላምና እርቅ እንዲፈጠር እና እርዳታ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲደርስ ያላቸውን ተስፋ አምባሳደሯና ብፁዕነታቸው ይጋራሉ።
Chargé d’affaires Ambassador Jacobson was honored to meet His Holiness Abune Mathias. They share a hope for peace and reconciliation and for aid to reach all Ethiopians in need. pic.twitter.com/H5RPnAOXkV
— U.S. Embassy Addis (@USEmbassyAddis) April 13, 2022
በኢትዮጵያ የዩናትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ባለሙሉ ስልጣን ተጠባባቂ አምባሳደር በመሆን በቅርቡ የተሾሙት ክብርት አምባሳደር ጃኮብሰን ከቅዱስነታቸው ቡራኬ ለመቀበል እና ይፋዊ የሥራ ትውውቅ ለማድረግ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ሲሆን በቅዱስነታቸውም አቀባበል ተደርጎላቸዋል ሲል የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ገልጿል። ቅዱስነታቸው ከክብርት አምባሳደሯ ጋር በነበራቸው ቆይታ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጡ ንግግር በኢትዮጵያ የሚቆዩበት ጊዜ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን የሚችሉበት ይሆን ዘንድ አባታዊ ምኞታቸውን ገልጸው በቡራኬ ሸኝተዋቸዋል ብሏል ልዩ ጽ/ቤቱ