የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ ብፁዕ አቡነ ማትያስን ማነጋገራቸው ተሰማ

[addtoany]

የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ  ጃኮብሰን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን መገናኘታቸው ተሰምቷል። በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መወያየታቸው ታውቋል። ሰላምና እርቅ እንዲፈጠር እና እርዳታ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲደርስ ያላቸውን ተስፋ  አምባሳደሯና ብፁዕነታቸው ይጋራሉ።

በኢትዮጵያ የዩናትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ባለሙሉ ስልጣን ተጠባባቂ አምባሳደር በመሆን በቅርቡ የተሾሙት ክብርት አምባሳደር ጃኮብሰን ከቅዱስነታቸው ቡራኬ ለመቀበል እና ይፋዊ የሥራ ትውውቅ ለማድረግ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ሲሆን በቅዱስነታቸውም አቀባበል ተደርጎላቸዋል ሲል የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ገልጿል። ቅዱስነታቸው ከክብርት አምባሳደሯ ጋር በነበራቸው ቆይታ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጡ ንግግር በኢትዮጵያ የሚቆዩበት ጊዜ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን የሚችሉበት ይሆን ዘንድ አባታዊ ምኞታቸውን ገልጸው በቡራኬ ሸኝተዋቸዋል ብሏል ልዩ ጽ/ቤቱ