ሜታ ኩባንያ የእርቃን ምስሎችን በማስላክ ሲያጭበረብሩ የነበሩ 63 ሺ አካውንቶችን አስወገደ።

ሜታ ኩባንያ የእርቃን ምስሎችን በማስላክ ሲያጭበረብሩ የነበሩ 63 ሺ አካውንቶችን አስወገደ።

የሜታ ኩባንያ መቀመጫቸውን በናይጄርያ ያደረጉና በማጭበርበር የተቀበሉትን የግለሰቦችን የእርቃን ፎቶ በመጠቀም ለማጥቃት ሲሞክሩ የነበሩ 63,000 የኢንስታግራም አካውንቶችን አስወግጃለው ብሏል።

እነዚህን አካውንቶች በመጠቀም ጥቃት የሚፈፅሙት ግለሰቦች የማህበራዊ ሚድያው ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶችን ግልፅ የሆኑ ምስሎች በተለያየ መንገድ እንዲልኩ በማታለል እና በማሳመን ይቀርባሉ።

ከዚህም በኋላ ይህን ተጠቅመው ገንዘብ ካልከፈሉ ወይም ፆታዊ ግንኙነት ካልፈፀሙ ምስሎቹን ይፋ እንደሚያደርጉ በማስፈራራት ሲፈጽሙ ነበር ብሏል።

ከቅርብ አመታት ወዲህ በናይጀሪያም ሆነ በተለያዩ ሀገራት ይህን መሠል ድርጊቶች መበራከታቸውን ሜታ ተናግሯል።

በተለይም ተጎጂዎቹ ከ14-17 አመት የሚሆኑ ታዳጊዎች ሲሆኑ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የዚህ ማህበራዊ ሚድያ ጥቃት ሰለባዎች ናቸው።

ኢንስታግራም በባለፈው ሚያዚያ ወር ወጣቶችን ከተለያዩ ፆታዊ ምዝበራዎች ለመጠበቅ አዳዲስ ስርዓቶችን እንደሚዘረጋ ገልፆ የነበረ ሲሆን በሙከራ ላይ ይገኛሉም ብሏል። አክሎም ተጠቃሚዎቹ  ከእነዚህ አይነት መጭበርበሮች እራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳውቋል።