ፕሬዚዳንት ፑቲን እና አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

ፕሬዚዳንት ፑቲን እና አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

ፕሬዝዳንት ፑቲን እና አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢትዮጵያ መንግስት ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ዜጎች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ፑቲን በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸውን መግለጻቸውንም በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል፡፡

አንቶኒዮ ጉተሬዝ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች ጥልቅ ሃዘን አንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

በጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደስር እንደሚችል ኦቻ መግለጹ ይታወሳል።