ከሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ስደተኝነት በአፍሪካ ቅጥረኛ ተዋጊ እስከመሆን

ከአስር ዓመታት በላይ በዘለቀው የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው በቱርክ ተጠልለው የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሌላ ጦርነት እየገቡ ነው። ሶሪያውያኑ ጦርነት ሸሽተው በስደት በችግር ውስጥ መሆናቸው ለቤተሰባቸው የሚያስፈልገውን ማድረግ አይችሉም። በዚህ አጋጣሚም በአፍሪካ ውስጥ ሥራ እንደተገኘላቸው በሚገልጹ ሰዎች አማካይነት በቅጥረኛ ተዋጊነት እንዲሰማሩ እየተደረገ ነው። …