የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ተሰማ፡፡

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ተሰማ፡፡
ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ ዩኒቨርስቲውን ለ13 አመታት አገልግለዋል፡፡

ይሁንና የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ መልቀቃቸውን ለዩኒቨርስቲው ማሳወቃቸውን ሰምተናል፡፡

በዩኒቨርስቲው የአለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ተወካይ ወ/ሮ ይዳኙ ማንደፍሮ ለሸገር እንደነገሩት ዶ/ር ደሳለኝ ስልጣናቸውን ለመልቀቃቸው ዝርዝር ምክንያት አልተናገሩም፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ በፕሬዝደንትነት ዘመናቸው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ውጤታማ እንዲሆን አስችለውታል ተብሏል፡፡

Image may contain: 1 person, suit