ስለ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ታጋች ተማሪዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

ስለ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ታጋች ተማሪዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

በታጣቂዎች ስለታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ፣ የግቢው የወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት እና የታጋች ቤተሰብን ምን አዲስ አለ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬም ጥያቄ አቅርቧል።

የታጋች ቤተሰቦች አጋቾቹ ወደ 20 የሚሆኑ ታጋቾችን ከትላንት ጀምሮ ወደ ማያውቁትና ጫካ በበዛበት ቦታ በቡድን ከፋፍለው በእግር እያጓጓዟቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህንን ነገር የሰሙት አጋቾቹ ደውለው ” ልጆቻችሁ እንዲለቀቁ ገንዘብ አምጡ ” ብለው በዛቱበት እና ከልጆቻቸው ጋር በስልክ በተገናኙበት ወቅት ነው።

አጋቾቹ ገንዘብ እንዲላክላቸው ፤ ለዚህም ትንሽ ጊዜ እንዲሰጡ ቢጠየቁም ለመስማት ፈቃደኞች እንዳልሆኑ የታጋች ቤተሰቦች ገልጸዋል።

የልጆቻቸው ደህንነት እጅግ በጣም በከፋ ጭንቀት ላይ እንደጣላቸው ገልጸው ልጆቻቸውን ወደ ሌላ አገር እንዳያስወጧቸው መከላከያ እና ፌደራል ፓሊስ ክትትል አድርገው እንዲታደጉላቸው ተማጽነዋል።

ቲክቫህ ያነጋገረው የወጌላዊያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረትን በበኩሉ፣ ትላንት መኪና እየጠበቁ የነበሩት መኪና አግኝተው ወደ ቤተሰብ ጉዞ ማድረጋቸውን ገልጿል።

ቀሪዎቹ ግን አሁንም ገንዘብ በታጋቾቹ እየተጠየቁ ነው ብሏል።

በታጋች ተማሪዎቹ ጉዳይ አዲስ ነገር አለ ? ሲል ቲክቫህ የጠየቃቸው የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አንድ አካል ፥ ለበላይ ሪፓርት ከማድረግ ውጪ ምንም ማድረግ እንዳልተቻለ ገልጸዋል።