የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ 4ኛ ቀኑን ይዟል::

በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ደረሰበት፡፡

በፓርኩ የተከሰተው የእሳት አደጋ 4ኛ ቀኑን ይዟል::

የአደጋው መንስኤ በውል ባይታወቅም አደጋውን አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የአደጋው መንስኤም እየተጣራ እንደሚገኝ የፓርኩ የስራ ኃላፊዎች ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ገልፀዋል ።

በፓርኩ ላይ የደረሰውን አደጋ መጠን የሚያጣራ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መላኩም ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው ፖሊስ ፣ መከላከያና ህብረተሰቡ በጋራ በመሆን ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረጉ መሆኑም ተመልክቷል፡፡