ጀነራል ተፈራ ማሞ በይፋ የህልውና ትግሉን ተቀላቀሉ !

ጀነራል ተፈራ ማሞ በይፋ የህልውና ትግሉን ተቀላቀሉ !

  • ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአማራ ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል በይፋ ተቀላቀሉ።
  • ጄኔራሉ ከሰው በላው አፈና ለጥቂት ማምለጣቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ዛሬም ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግልን በይፋ መቀላቀላቸውን ከፋኖ አመራሮች አረጋግጠናል።በአዲስ አበባ ከተማ ከቤተክርስቲያን መልስ በእግር ጉዞ ላይ እንዳሉ በ”ኮሬ ነጌኛ” ገዳይ ቡድን የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው የነበረው ጀኔራል ተፈራ ማሞ፣ ከግድያ ሙከራው ወታደራዊ ጥበባቸውን ተጠቅመው በማምለጥ አሁን ላይ በይፋ የአማራ ፋኖን ትግል መቀላቀላቸውን ኢትዮ 251 ሚዲያ ከፋኖ አመራሮች አረጋግጣለች፡፡

የጄኔራል ተፈራ ማሞ ይፋዊ በሆነ መንገድ የአማራ ፋኖን ትግል መቀላቀል የሕልውና ትግሉን በሞራል፣ በወታደራዊ አመራርና በሕዝባዊነቱ ላይ ከፍ ያለ መነቃቃት እንደፈሚፈጥር ይጠበቃል፡፡

ጀኔራል ተፈራ ማሞ ገና ከአፍላ ዕድሜቸው ጀምሮ፣ ከ40 ዓመት በላይ የወታራዊ አመራር ልምድ ባለቤትና የሸማቂ ኮማንዶ መሪ በመሆን ወርቃማ የትግል ሕይወት ያሳለፉ ግንባር ቀደሙ ከፍተኛ መኮንን ናቸው፡፡

ከጀኔራል አሳምነው ጽጌና ሌሎች የትግል ጓዶቻቸው ጋር በመሆን የአማራ ልዩ ኃይልን በማደራጀትና የተዋጊነት አቅሙን በማሳደግ በአማራ ሕዝብ ትግል ውስጥ ልዩ ታሪክ መስራታቸው ይታወቃል፡፡

ጀኔራሉ፦ በኮማንዶ ሥልጠና፣ ኢንዶክትሪኔሽን፣ የአደረጃጀት፣ ወታደራዊ ስምሪት፣ ሎጀስቲክስ፣… ቅኝት፣ ተልዕኮ፣ ግዳጅ አፈጻጸም፣ ወታደራዊ ግምገማ፣ መልሶ ማደራጀት፣ የሽምቅ ውጊያ፣ የግንባር ፍልሚያ፣ የአንገት ቦታ ቁጥጥር፣ ገዥ መሬትን ቀድሞ መያዝ፣ ምሽግ ሰበራ፣ … የተካኑቸው ወታደራዊ ጥበባቸው እንደሆኑ በቅርብ ጓዶቻቸው የተመሰከረላቸው ናቸው።ጀኔራል ተፈራ ማሞ በይፋ የአማራ ፋኖን ትግል መቀላቀል ተከትሎ የመጀመሪያው ጀኔራል ያደርጋቸዋል፡፡  በጀኔራሉ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን በመከታተል ትኩስ መረጃዎችን  ማድረሳችንን እንቀጥላለን፡፡