ቱርክ፣ ኢትዮጵያንና ሱማሊያን ማደራደር ጀመረች

ቱርክ፣ ኢትዮጵያንና ሱማሊያን በባሕር በር ውዝግባቸው ዙሪያ ዛሬ አንካራ ውስጥ እንዳደራደረች ከባለሥልጣናት ምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

ኾኖም ኹለት ለድርድሩ ቅርብ የኾኑ ምንጮች የድርድሩ ግብ ምን እንደኾነ ግልጽ እንዳልኾነና ከድርድሩ ኹነኛ ውጤት የመገኘቱ እድሉ ዝቅተኛ መኾኑን መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ፣ ሱማሊያና ቱርክ ባለሥልጣናት በቱርክ-መራሹ ድርድር ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት እንደተቆጠቡ ዜና ምንጩ ገልጧል።

የሶማሊላንድ ራስ ገዝ መንግሥት ቃል አቀባይ ግን፣ ሶማሊላንድ በቱርክ አደራዳሪነት በሚካሄደው ድርድር ውስጥ ተሳታፊ እንዳልኾነች ተናግረዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ከሱማሊያ ጋር በቱርክ አመቻቺነት ዛሬ ይደረጋል ስለተባለው ንግግር ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያለው ነገር የለም።