ፋኖን ለመምታት በሚል በብልፅግና እና ትህነግ መካከል አዲስ የጓዳ ስምምነትም ተፈፅሟል።

ፋኖን በሌላ እቅድ “አጠፋዋለሁ” ብሎ የነበረው ብልፅግና “ህወሓት ያግዘኝ” ብሎ መጥቷል። ፋኖን ለመምታት በሚል በብልፅግና እና ትህነግ መካከል አዲስ የጓዳ ስምምነትም ተፈፅሟል። በዚህም መሰረት፦
1)ወደ ራያ ከገባው በተጨማሪ በቀጣይ ቀናት በጠለምት የታጠቀ የትህነግ ኃይል እንዲገባ ተወስኗል።
2) የሰላም ስምምነቱ አካልና የህዝብ ጥያቄ ነው እንዲባል በትግራይ ከተሞች ሰልፎች ተደርገዋል። ጠለምት ላይ የተጠራ ተቃውሞ በአገዛዙ ታፍኗል።
3) ህወሓት “ፋኖን ትደግፋለህ” በሚል በብልፅግና ሲታማ የነበረበትን አጠራለሁ በሚል ሰሞኑን በተደረገው ጉባኤው ወስኗል። “ከኤርትራ ጋር እንተባበር” የሚል አጀንዳ ውድቅ ተደርጎ “ከአብይ ጋር ተባብረን። የሚለንን ፈፅመን የድርጅታችን እውቅና እና ወልቃይትና ራያን እንረከባለን” ብለዋል።
4) በየጊዜው ከእቅድ ወደ እቅድ ሲሸጋገር የከረመው ብልፅግና ይህኛውን እቅድ ሰሞኑን ይጀምረዋል። ጉዳዩን የተቃወሙ የዞንና የወረዳ አመራሮች ተጠርተዋል።
5) ከትህነግ ታጣቂ በተጨማሪ አዴን በሚል ከወራት በፊት ከብአዴን ጋር የተስማማ ታጣቂው ሰሞኑን በአገዛዙ ድጋፍ ስልጠናዬን ጨርሻለሁ ብሏል።
ወደ ላስታና አጎራባች አካባቢዎች አሰማራዋለሁ ብለው አስበዋል።