አማጋ የስፖንጅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 23 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደረሰ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አማጋ የስፖንጅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 23 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡

Image may contain: one or more people, cloud, sky and outdoorበእሳት አደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካካል ስምንቱ የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ሰራተኞች ናቸው።

15ቱ ደግሞ የፋብሪካው ሰራተኞች መሆናቸውን የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባላስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡

አደጋው የደረሰው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍል ከተማ ወረዳ አምስት የኢንዱስተሪ ዞን አማጋ የስፖንጅ ፋብሪካ ላይ መሆኑን አቶ ንጋቱ ገልጸዋል፡፡

በአደጋው አብዛኛው ፍብሪካው ክፍል መውደሙን የገለጹት የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ ፋብሪካው የሚጠቀማቸው ግብዓቶች ተጠቀጣጣይ መሆናቸው አደጋውን አባብሰውታል ብለዋል፡፡

አደጋው 4 ሰዓት ተኩል ላይ የተከሰተ ሲሆን÷ 11 ተሽክርካሪዎችን፣ ሁለት አምቡላንሶችን፣ 85 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችን ያሰማራው ባለስልጣኑ በ4 ሰዓታት ውስጥ እሳቱን ለመቆጣጠር ችሏል፡፡

98 ሺህ ሊትር ውሃ፣ 25 ሺ ሊትር ኬሚካል እሳቱን ለማጥፋትና ለመቆጣጠር አግልግሎት ላይ ውሏል፡፡