የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ይበልጥ ሊሻሻል እንደሚገባ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አሳሰበ

DW : አምነስቲ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ የሚካሄደውን ለውጥ አድንቆ ፣ አሳሳቢ ያለው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግን ይበልጥ ሊሻሻል እንደሚገባ አሳስቧል። ከበፊቱ የተሻለ ነው ሲል የገለጸው አዲሱ የሲቪል ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ የተወሰኑ አንቀጾችም አሁንም ተጽእኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ስጋቱን ገልጿል።

Image result for አምነስቲ ኢንተርናሽናል

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በለውጥ ሂደት ላይ በምትገኘው በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ይበልጥ እንዲሻሻል ጠየቀ። አምነስቲ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ጥሪ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ በወሰዷቸው የለውጥ እርምጃዎች አድንቆ ፣ ሆኖም አሳሳቢ ያለው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ይበልጥ ሊሻሻል እንደሚገባ አሳስቧል። ከበፊቱ የተሻለ ነው ሲል የገለጸው አዲሱ የሲቪል ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ የተወሰኑ አንቀጾችም አሁንም ተጽእኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ያለውን ስጋት ገልጿል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት በበኩሉ አዲሱ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች አዋጅ ተገቢ ዝርዝር ጥናት የተደረገበት እና የማያሰራም እንዳልሆነ አስታውቋል።