በዶክተር አብይ የሚመራው ኦሕዴድ/ኦዴፓ የአዲስ አበባ እና የአፋን ኦሮሞ ጉዳዮች ለመመለስ እየሰራሁ ነው አለ

Taye Dendea (Geberu Godane )

DW : የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ «ODP» ሕገ-መንግሥቱ እየተናደ ነው ፡ ፌዴራሊዝሙ ፈርሷል ፡ አሃዳዊ ስርአት ለመመስረት እየተሠራነው የሚሉ እና ሌሎች የሃሰት ፕሮፖጋንዳዎች በመገናኛ ብዙኃን ፡ ምሁራን እና ማህበራዊ መገናኛዎች መከፈታቸውንና ይህንንም እንደማይቀበለው ለ«DW»ተናገረ፡፡
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ «ODP» ሕገ-መንግሥቱ እየተናደ ነው ፡ ፌዴራሊዝሙ ፈርሷል ፡ አሃዳዊ ስርአት ለመመስረት እየተሠራነው የሚሉ እና ሌሎች የሃሰት ፕሮፖጋንዳዎች በመገናኛ ብዙኃን ፡ ምሁራን እና ማህበራዊ መገናኛዎች መከፈታቸውንና ይህንንም እንደማይቀበለው ለ«DW»ተናገረ፡፡ ሕገ- መንግሥቱ እስካልተስተካከለ እና በሥራ ላይ እስከሆነ ድርስ መከበር አለበት ፡ ፌዴራሊዝም ለሀገሪቱ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በዚህ ላይ ድርድር እንደሌለውም የፓርቲው ማእከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት የህዝብ አስተያየት እና ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታየ ደንደአ ለDW ተናግረዋል፡፡ ፓርቲው የኦሮሞ ህዝብ የረጅም ጊዜ ጥያቄዎች ናቸው ያላቸውን የአዲስ አበባ እና የአፋን ኦሮሞ ጉዳዮች ለመመለስ እንደሚሠራም ኃላፊው የተናገሩ ሲሆን አፋን ኦሮሞ የፌዴራል ቋንቋ ይሁን የሚለው የፓርቲያቸው ብቻ ሳይሆን የሌሎች ፓርቲዎችና  የህዝቡ ጥያቄ በመሆኑ ጥያቄው እንዲመለስ እንሠራለን ብለዋል፡፡  በአዲስ አበባ ጉዳይም ሌሎችን የከተማዋን ነዋሪዎች ጥቅም በማይጎዳ መልኩ የሚነሱ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎችን እንመለከታቸዋለን ብለዋል፡፡