በቅርቡ ማቋቋሚያ አዋጁ በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀውን የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን የትግራዩ ተቃዋሚ ፓርቲ አረና ትግራይ ተቃወመ።
አረና ትግራይ ለሉዓላዊነት እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ትናንት በሰጠዉ መግለጫ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ሙሉ በሙሉ አለመከብርና የዜጎች መፈናቀል አሳሳቢ መሆኑን አስታወቋልም።ሕዝባዊ ወያኔ ሕርነት ትግራይ የሚቆጣጠረዉ የትግራይ ምክር ቤት የአስተዳደርና ወሰንና የማንነት ጉዳይ ከሚሽን መቋቋሙን ተቃዉሞታል።
ተቃዋሚዉ ፓርቲ አረና ትግራይም አዲሱን ኮሚሽን ኢ-ህገመንግሥታዊ ሲል ተቃውሟል። ኢህአዴግ ብቻውን አገሪቱን ወደ ተረጋጋ ሰላም እና ዴሞክራሲ ሊያሸጋግር አይችልም ያለው አረና ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት እንዲመሰረትም ጠይቋል።