በኦሮሚያ 20 ንጹሃን በመንግሥት ወታደሮች የጅምላ ግድያ ተፈጸመባቸው

ኦነግ፣ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቶሌ ወረዳ የመንግሥት ወታደሮች ሰሞኑን በፈጸሙት ጥቃት 20 ንጹሃን የጅምላ ግድያ እንደተፈጸመባቸው አረጋግጫለሁ በማለት ትናንት ባወጣው መግለጫ ከሷል።

ግንባሩ፣ የሟቾችን ስም ጭምር ዘርዝሯል። መንግሥት በክልሉ የንጹሃን ዜጎችን ደም ማፍሰስን የዕለት’ተለት ሥራው አድርጎታል ያለው ኦነግ፣ የጅምላ ግድያው እንዲቆምና የዜጎች ደኅንነት እንዲጠበቅ ተደጋጋሚ መግለጫ ባወጣም ችግሩ እየባሰ ሄዷል ብሏል።

ኦነግ፣ ግድያዎች እንዲቆሙ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ሲቪል ማኅበራት ጫና እንዲያደርጉ ጠይቋል።