በሸዋ ፋኖ ዕዝ በተሰራ ድንቅ ኦፕሬሽን አንድ የስርዓቱ አገልጋይ ባንዳ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የዐማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ድንቅ ኦፕሬሽን!

ከአዲስ አበባ በ130 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሸዋ ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ ትላንት ማለትም መጋቢት 19/2016 ዓ.ም ሌሊት በሸዋ ፋኖ ዕዝ በተሰራ ድንቅ ኦፕሬሽን አንድ የስርዓቱ አገልጋይ ባንዳ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ይህ ባንዳ የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘደንት ሲሆን ዶ/ር የሚባል የግዢ ዱክትርና ይዞ ለስርዓቱ አሽከር በመሆን ስልጣኑን ተጠቅሞ በዩኒቨርሲቲው የአማርኛ ትምህርት እንዳይሰጥ ያገደ፣ የታሪክ ዲፓርትመንትን ያገደ፣ የተቋሙን በጀት ለ”መከላከያ” ያዋለ፣ ተቋሙ እንደ ማሰልጠኛ እና ካምፕ እንዲያገለግል የፈቀደ፣ የግቢውን ታሪካዊ ነገሮች በሙሉ ያፈረሰና እያፈረሰ ያለ ከየትኛውም የብልፅግና ከፍተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ አመራሮች ያልተናነሰ ነውረኛ ተግባር በአማራውያን ላይ የፈፀመ ባንዳ ነው።

ይህን ነውረኛ በትላንትናው ዕለት በደብረ ብርሃን ከተማ ሌሊት ላይ የዐማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በቁጥጥር ስር አውሎታል።