በለሊት በአራዳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ የተፈጸመ ነውር !!!

በለሊት በአራዳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ የተፈጸመ ነውር!!!

ጥር 30 ዕለተ ሐሙስ ከምሽቱ 6:00 ሰአት ላይ ያለ ማዘዣና ያለ ዕውቅና ሕግን በተላለፈ መልኩ በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ የየፖሊስና የፌደራል ልብስ የለበሱ ጥይት የታጠቁ አካላት ሰተት ብለው በመግባት ድፍረት የተመላበትን ተግባር ፈጽመዋል!

የዕለቱን የጥበቃ አካላት በማስፈራራትና በመዛት “በቤተክርስቲያኑ ውስጥ መሳሪያ ተቀምጧል” በሚል የዲያቆናትና ካህናትን ቤት ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ እየበረገዱ ሕጋዊ የሆኑ (የቤ/ክ ሎጎ ያለባቸውን) ባንዲራዎች እያወረዱ በመውሰድ እንዲሁም በአካባቢው ምዕመናን የተገዙ ከ250 ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን የቤ/ክ ሎጎ ያለባቸውን ብዛት ያላቸውን ባንዲራዎች : የታቦት ማሳመሪያ የዲኮር ዕቃዎች በእግር እየረገጡ ክብራቸውን ባዋረደ መልኩ ተወስደዋል!

የፖሊስና የፌደራል አካል ነን ብለው የመጡት አካላት ግቢውን በሚያውክ መልኩ ስለገቡ በጊዜው የነበሩ አካላት ወደ አስተዳዳሪው በመደወላ እንዲመጡ ለመደረግ የቻለ ቢሆን የሕግ አካላት ነን ያሉት ግን አስተዳዳሪውን በማዋከብና ለብዙ ዓመታት የቤ/ክ እና የሀገር ቅርስ ያለበትን ሙዚየም ክፈቱ እስከማለት ለመጠየቅ ችለዋል የደብሩ አስተዳዳሪ ግን ” ሕዝብና አገልጋዮች በሌሉበት ለዚያውም በዕኩለ ሌሊት አልከፍትም” በማለት አቋማቸውን አሳይተዋል!

ይህ የቤ/ክን እና የምዕመናንን ክብር ባልጠበቀና እንደ ወንጀለኛ በዕኩለ ሌሊት መፈጸሙ ነውር ሆኖ ሳለ በካህናትና ዲያቆናቱ ላይ የተፈጸመው እንግልት ደግሞ እጅጉን አሳፋሪ ነበር በጊዜውም የነበሩ የአይን ምስክሮች እንደነገሩን አንዳንድ ካህና በተፈጸመው አዝነው አምርረው እስከማልቀስ ደርሰዋል!

በቀጣይነትም ዳግም ይህ ነገር ለመፈጸሙ ምንም ዋስትና ስለሌለን የቤ/ክኑ አስተዳደር አካል ; የሰ/ት/ቤቱ አመራር ; የአካባቢው ወጣትና ምዕመናን በጋራ በመሆን ጉዳዩን በባለቤትነት የፈጸሙት አካላት የወሰዷቸውን ንብረቶች እንዲመልሱና የፈጸሙት የቤ/ክንን ክብር የተላለኀ መሆኑን እስከ ሚመለከት አካል ሔደው ሊጠይቁ ይገባል!

አሁን ላይ ማንም እየተነሳ መሳሪያ አንግቦ ሕገ መንግስቱን በተጻረረ መልኩ ቤ/ክ ድረስ ገብቶ የፈለገውን ነገር እያደረገ ነገም ካህናት ብቻ የሚነኩትን ቅዱሱን ታቦትና ንዋየ ቅዱሳቱን ላለመንካቱ ምንም ዋስትና የለንም!

የደብሩ አስተዳደር የሰንበት ት/ቤቱ አመራርና አባላት የአካባቢው ወጣቶችና ምዕመናን በሀላፊነት ከመላው ምዕመን ጋር የተፈጸመውን ተግባር አውግዘን የተወሰዱ ንብረቶች እንዲመለሱ የተፈጸመውን ተግባር ልንጋፈጥ ይገባናል!
ስለ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ያገባኛል

@ Eyob Bekele