የወደብ ዜናው ሐሰት ነው፤ ሕዝቤን በአጀንዳ በመጥመድ ሰቅዞ ለመያዝ የተፈበረከች ቀሽም ሴራ ናት። ( ዘመድኩን በቀለ)

“…የወደብ ዜናውም ሐሰት ነው። ሰሞኑን ከቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግሥ መልስ ኦሮሙማዎቹ ለጨፈጨፏቸው ኦርቶዶክሳውያን አጀንዳ ማስቀየሻና ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ከተማን ባለቤትነት በጉልበት የኦሮሚያ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ስላሉ ሕዝቤን በአጀንዳ በመጥመድ ሰቅዞ ለመያዝ የተፈበረከች ቀሽም ሴራ ናት።

“…እናም የወደብ ዜናው የኦሬክስ ማጨናበሪያ፣ ማደናገሪያም ኦዱ ናት። 20 ኪሜ ወደብ በሊዝ መከራየት የወደብ ባለቤት አያስደርግም። ኦሮሙማዎቹ ለሶማሊላንድ በምትኩ የሰጡትን ነገርም አልተነፈሱም። በዓለም ላይ ሱማሌ ላንድን እንደ ሀገር እውቅና እንሰጣለን ነው ያለው መሃይሙ አቢይ አህመድ። እሱም ቢሆን ገና የመግባቢያ ሰነድ ነው የተፈራረሙት። በእንግሊዝኛ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረምን ብሎ መግለጫ ያወጣው አረመኔው የሐሰት አባት መጀመሪያ በአማርኛ ቀጥሎ ከ11:ሰዓት በኋላ በኦሮምኛ ቢበጠረቅም በእንግሊዝኛ ግን አልተነፈሳትም። ኢቲቪም ሰበር ዜናውን አርሟል። edit history ላይ ገብታችሁ እዩት። ምስኪን ኦሮሞዎች ግን በገጠር ኦሮሞ ወደብ አገኘ ብለው ሲጨፍሩ ማምሸታቸው ነው የተነገረው።

“…በሰላም ወጥቶ በማይገባበት፣ በኦሮሚያ ውስጥ ዐማራና ኦርቶዶክስን መጨፍጨፍ፣ የግለሰቦች መኪናን በኦሮሚያ እንደ ችቦ ማንደድ በማያስጠይቅበትና ሀገሪቷ መንግሥት አልባ በሆነችበት ዘመን በዚህ በፌክ የወደብ አገኘን ዜና አጨናብሮ ማለፍ አይቻልም። ለማንኛውም በዚህ የአማርኛና የኦሮሚኛ ዜና ጉዳይ የሶማሊያ መንግሥት ፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል። በዘመነ ኦሮሙማ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ አፈር ከደቼ ግጧል። ኦሮሙማ በኢትዮጵያ ዙሪያ ካሉ ሀገራት ጋር ዙሪያውን እሳት ጭሮ ተቀምጧል። በሀገር ውስጥም ከሁሉም ብሔር ጋር ተናክሷል። መጨረሻውን እንጃለቱ። ዳፋው ግን ለስደተኛው ኦሮሞ ነው የሚተርፈው።

•እረፍቴን አልጨረስኩም።