ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የጊዴቦ ግድብ ስራ ፕሮጀክትን ዛሬ ጥር 26 ቀን 2011 መረቁ:: በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች የሚገኘው ይህ ግድብ 25.8 ሜትር ከፍታና 335 ሜትር ርዝመት ይለው ሲሆን ከ62.5 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ውሃ የመያዝ አቅም አለው:: ሰርቶ ለማጠናቀቅም ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ፈጅቷል:: በዛሬው ምረቃ ስነስርዓት ላይም የኦሮምያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ለማ መገርሳና የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሚሊዮን ማቲዎስ ተገኝተዋል::
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የጊዳቦ ግድብ ፕሮጀክት የምእራብ ጉጂና ሲዳማ ዞን ህዝቦችን ያቀራረበ መሆኑን አንስተዋል:: የኢትዮጵያ መንግስት ለግብርናና የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለማልማት በሰጠው ትኩረት መሰረትም ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ማህበረሰቦችን የሚያቀራርቡ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች እንደሚቀረፁ አስታውቀዋል::በመጨረሻም ጠ/ሚሩ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ከመጠየቅ አልፈው የተገኙ ድሎች ላይበመንተራስ ለአገራቸው እድገት የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል::