የርዕሠ-መስተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ የሕግና የሠብአዊ መብት ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጀማል ድሬይ እንደሚሉት አራተኛ ወሩን የያዘዉን መስተዳድር ለማፍረስ የቀድሞ ባለሥልጣናት፣ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የኢሶሕዴፓ ሊቀመንበር ና የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ባለሥልጣናት ባንድ አብረዉ እየዶሎቱ ነዉ።
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሠ መተዳድር የአብዲ መሐመድ ዑመር ደጋፊዎች አዲሱን የክልሉን ርዕሠ መስተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ ዑመርን ከስልጣን ለማዉረድ እያሴሩ መሆናቸዉን አንድ የክልሉ ባለስልጣን አጋለጡ።የርዕሠ-መስተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ የሕግና የሠብአዊ መብት ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጀማል ድሬይ እንደሚሉት አራተኛ ወሩን የያዘዉን መስተዳድር ለማፍረስ የቀድሞ ባለሥልጣናት፣ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የኢሶሕዴፓ ሊቀመንበር ና የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ባለሥልጣናት ባንድ አብረዉ እየዶሎቱ ነዉ።የሕግና የሰብአዊ መብት አማካሪዉ አክለዉ እንዳሉት ከሴረኞቹ መካከል አንዳዶቹ በፌደራሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ክስ የተመሠረተባቸዉ ናቸዉ።