­

” ያለፈው ዘመን ይበቃ ዘንድ ስለሰላም ልንጸልይ ይገባል ” – ብፁዕ አቡነ አብርሃም

[addtoany]

” ያለፈው ዘመን ይበቃ ዘንድ ስለሰላም ልንጸልይ ይገባል ” – ብፁዕ አቡነ አብርሃም

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ ” እንደቀድሞ ጊዜ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን እያለች #ሰላም ከሀገር አይርቅም ነበር፤ ዛሬ በእኛ በአገልጋዮቿ ምክንያት ያን ሚናዋን አጥታለች ” አሉ።

ብፁዕነታቸው ይህን ያሉት በ ” ማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ ” ላይ ተገኝተው ቡራኬና ቃለ ምእዳን በሰጡት ወቅት ነው።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በወቅታዊ የሀገሪቱ የሰላም ሁኔታ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፥ ” “ቤተ ክርስቲያን አንድ ሁኑ ብላ ታስተምራለች ፤ ጥላቻን መገዳደልን ታወግዛለች፤ በንግግር በውይይት ፍቱ ትላለች ” ብለዋል።

” ይህንን አቋሟን በበጎ የማይመለከቱ ግን ይኖራሉ ” ሲሉ ተናግረዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ ” እንደቀድሞ ጊዜ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን እያለች ሰላም ከሀገር አይርቅም ነበር፤ ዛሬ በእኛ በአገልጋዮቿ ምክንያት ያን ሚናዋን አጥታለች ” ያሉ ሲሆን ” ወላዋይና አድርባዮች ስለሆንን፣ ምን አገባኝ ብለን መስለን ስላለን ሀገሪቱን ዋጋ እያስከፈልን ነው፤ የወገን ደምም ሲፈስ ማየት ተለምዷል ” ሲሉ ገልጸዋል።

” ያለፈው ዘመን ይበቃ ዘንድ ስለሰላም ልንጸልይ ይገባል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የማህበረቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።