የዐብይ አህመድ ቅጥረኛ ወታደሮች!

የዐብይ አህመድ ቅጥረኛ ወታደሮች!
አማራ ንፁሃን ላይ ከባድ መሳርያ እየተተኮሰ ንፁሃን በጅምላ እያለቁ ነው። ሸዋ (ለሚ)፣ ደብረማርቆስና ደብረታቦር በርካታ ንፁሃን በከባድ መሳርያ አልቀዋል። ተቋማት ወድመዋል። የአርሶ አደሩ ቤትና እንሰሳት በከባድ መሳርያ ሆን ተብሎ እየተመቱ ነው። ይህን የአማራ ሕዝብ ከቁስል አድኖ የላካቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጭምር ያማረረ ነው። ብዙዎች መሳርያቸውን እየሸጡ ጠፍተዋል። ይህን የሚያደርጉ የዐብይ ቅጥረኞች ግን ሞልተዋል። መደበኛ መከላከያ ሆነው በጥላቻ ከተሰበኩት ባሻገር ቅጥረኛ ሰራዊት ተሰማርቷል።
አንዱና የመጀመርያው ከህወሓት ጋር በነበረው ጦርነት በመላ ኢትዮጵያ ታስረው የነበሩ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ ናቸው። አብይ ሲያስገርፋቸው ከርሞ አሁን በገንዘብ ገዝቶ አማራ ሕዝብ ላይ የዘር ፍጅት እንዲፈፅሙ እያደረገ ነው።
የትግራይ ተወላጆች የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበሩት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አልተፈቱም ነበር። አማራውን ለመውጋት ሲል ፈትቷቸዋል። የታሰሩበት ሁለት አመት ስራ ላይ እንደነበሩ ተቆጥሮ የሁለት አመት ደሞዝ ተከፍሏቸዋል። እድገት ተጠብቆላቸው ስራ ላይ እንደነበሩ ተደርጎ በሁለት አመት ያገኙት ነበር የተባለው ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ይህ በግልፅ ቅጥረኝነት ነው።
በቅርቡ ደግሞ ወደ ትግራይ 20 ሺህ የሚደርስ የመከላከያ ዩኒፎርምና ጫማ ተልኳል። ትህነግ ያሰናበታቸውንም ሆነ በካምፕ ያሉትን ወደ አማራ ክልል ሊያመጣ እንደሆነ ተገምቷል።
ከኦነግ ሸኔ ተማረኩ እያሉ የሚያሳዩትን፣ በየ ክልሉ ጡረታ የወጡትን ሳይቀር የአመታት ደሞዝ ከፍለው አማራ ክልል ላይ አሰማርተዋል። እነ ሽመልስ የፈጠሩት የኦነግ ሸኔ ክንፍን እንደሚጠቀሙበት ይታወቃል።
የአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በገንዘብ በተገዙ ወታደሮች ጭምር ነው። በየትኛውም ዓለም በገንዘብ የሚገዙ ወታደሮች ከተገኙ ያመጧቸዋል። ይህ በግልፅ ሆን ተብሎ ሕዝብን ለመምታት የተደረገ ዘመቻ ስለመሆኑ ማሳያ ነው።