በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን የሚገኙ ከመሀል ሀገር ከተሞች የሚያገናኙ መንገዶች ለወራት ተዘግተው እንደሚገኙ ተነገረ

በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን የሚገኙ የቤሮና የማጂ ወረዳዎችን ከዞኑና ከመሀል ሀገር ከተሞች የሚያገናኙ መንገዶች ለወራት ተዘግተው እንደሚገኙ እየተነገረ ይገኛል፡፡ የየወረዳዎቹ ነዋሪዎች ለዲ ደብሊው እንደገለጹት መንገዶቹ የተዘጉት በአካባቢው በሚገኙ ጎሳዎች መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ነው፡፡

 

በወረዳዎቹ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ሄድ መጣ እያለ በተከሰተው ግጭት አስከአሁን ከስልሳ በላይ ሰዎች ሲሞቱ በመቶዎች

የሚቆጠሩ ለጉዳት መዳረጋቸውን በቤንች ማጂ ዞን የቤሮ ወረዳ መስተዳድር አስታውቋል፡፡ በአሁኑወቅት ግጭቱን ለማስቆምና የተዘጉ መንገዶችን ለማስከፈት የጎሳ መሪዎችንና ባህላዊ የአገር ሽማግሌዎችን ያሳተፈ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ የመስተዳድሩ የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡