24 ሚሊዮን ብር የሚገመት በመንግስት ገንዘብ ላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉት ኤርሚያስ አመልጋ ፍርድ ቤት ቀረቡ

የአክሰስ ሪል ስቴትና የዘመን ባንክ መሥራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት አርብ ጥር 3 ቀን 2011 ዓ.ም ቢሆንም ጉዳያቸው በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት የታየው ዛሬ ረፋዱ ላይ ነው።

አቶ ኤርሚያስ ፍርድ ቤት የቀረቡት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በሸጡት የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ጋር በተገናኘ መሆኑ ታውቋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ 51 ሚሊዮን ብር ግምት ያለውን ኢምፔሪያል ሆቴል በ75 ሚሊዮን ብር ለሜቴክ በመሸጥ፣ 24 ሚሊዮን ብር የሚገመት በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው መጠርጠራቸውን ነው ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ የገለፀው፡፡