የማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ ላይ የጥላቻ እና አጸያፊ ንግግሮች-የኢትዮጵያውንን ቀጣይ ጊዜ ፈተናዎች

በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛዎች ላይ የሚሠራጩ የጥላቻ እና በአንድ ሰው የብሔር እና ሌሎች ማንነቶች ላይ የሚሰነዘሩ አጸያፊ ንግግሮች፣ ከወዲሁ የማይገቱ ከኾነ፣ ለኢትዮጵያውያን ቀጣይ ጊዜ ፈተና እንደሚኾኑ፣ አንድ ምሁር አሳሰቡ።

በሚሲሲፒ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል መምህር ዶር. ዘነበ በየነ፣ ችግሩ ከመሠረቱ ታውቆ መቀረፍ እንዲችል፣ እያንዳንዱ ግለሰብ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚገባው…