አየርላንድ ለላሊበላ ቅርስ ጥበቃ ድጋፍ ልታደርግ ነው

አየርላንድ ለላሊበላ ቅርስ ድጋፍ ልታደርግ ነው
የአየርንላድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮቫራድካር ከኢትዮጵያ የላሊበላን ጥንታዊ አብያት ክርስቲያናትን ቅርሶች በአረንጓዴ ብርሃንና በስራ ዕድል ፈጠራና በቅርስ ጥበቃ ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግና አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን ይፋ አደረጉ።

የአየርንላድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮቫራድካር የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን ጉብኝት ሲያደርጉ እንደገለጹት አገራቸው በቅርስና ጥበቃ ዙሪያ ያላቸውን ልምድና ከህሎት ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡

በላሊበላ አቢያተ ክርስቲያናት አካባቢዎች በስራ ፈጠራ የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ ለሚያደርግ በሚደረገው ጥረትም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናገረዋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው እንደገለጹት እንደ ላሊበላሉ ያሉ የባህላዊ ቀርሶች በሙያዊ ድጋፍ ለማድረግና በቱሪስት ተደራሽ ስፍራዎች ወጣቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ ነው፡፡በተለይ ላሊበላ ምሽት ላይ ጨለማ ነው።

እነሱ እየተጠቀሙበት ያለውን አረጓዴ ብርሃን ይህንን ቴክኖሎጂ በላሊበላና በአክሱም፤ሀረር በመተግበር ቅርሶን የብርሃንና የማራኪ ገጸታ በማላበስ ቱሪስቶችን የመቆያ ጊዜ ማራዘም ይቻላል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የላሊበላን አብያተ ክርስቲያናት ቅርሶችን መጎብኝታቸው በገጠር ወጣቶች ስራ ፈጠረና ቅርስ አጠባበቅ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የሶስት ዓመታት ስምምነት እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የላሊበላን አብያተ ክርስቲያናት ማለትም ቤተ ጊዮርጊስና ቤተ መድሀኒያለምን ጎብኝተዋል፡፡ካህናትም በሀይማኖታዊ ስርዓተ አቀባበል አድረገውላቸዋል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE