የተፈፀመው ጭፍጨፋ ዓለምአቀፋዊ ወንጀል ነው! – የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ

No photo description available.የተፈፀመው ጭፍጨፋ ዓለምአቀፋዊ ወንጀል ነው!
*****
በደብረ ኤልያስ አጼ መልክአ ሥላሴ ገዳም ባሉ ገዳማውያን መነኮሳት፣ ገዳሙ የሚያሳድጋቸው ሕፃናት እና መንፈሳዊ ፈውስን ፈልገው በገዳሙ በነበሩ ፀበልተኞች ላይ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የፈፀሙትን ከሕግ ውጭ የሆነ ጭካኔ የተሞላበት ግድያ በጽኑ አወግዛለሁ።
ራሱን «የጋራ የፀጥታ ግብረ ኃይል» እያለ የሚጠራው ቡድን የኢፌዴሪ ሕገመንግስትንና ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች በሚገረስስ መልኩ ባልተመጣጠነ፣ ያለ ልዩነት፣ ጭካኔ በተሞላበት አኳኋን እና ከሕግ ውጭ የፈፀማቸው ግድያዎች የ«ማንነት ተኮር ጅምላ ጭፍጨፋ» እና «ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት» ተብሎ የሚወሰድ ነው።
መላው ኢትዮጵያውያን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡና ሚዲያዎች ይህንን አስነዋሪ ድርጊት በጽኑ እንድታወግዙትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጫና ታደርጉ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ።