በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ደማቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በዳንሻ ከተማ ደማቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

በተካሄደዉ ህዝባዊ ስላማዊ ሰልፉ ላይ የአማራ ነን አልን እንጂ አማራ እንሁን አላልነም፤ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ የፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነዉ።

✔️- የማይገባን አልፈን አንጠይቅ፤ የራሳችንም አሳልፈን አንሰጥም። በማንነታችን/በአማራነታችን በርስታችን አንደራደርም የራሳችንም አሳልፈን አንሰጥም!!

✔️- የፖለቲካ ሴራ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ለድጋሜ እልቂት እንጂ ሰለምን አያመጣም የሚሻለዉ መራራዉን ሀቅ መቀበል ብቻ ነዉ።

✔️-ለእንግዶሽ እንጂ ለወንጀለኞች ቦታ የለነም፣ በወልቃይት ጠገዴ የተፈጸሙ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፍትህ ካሳ ንፈልጋለን፣

✔️-ተበዳይ እንጂ በዳይ ተጨፍጫፊ እንጂ ጨፍጫፊ፣ተወራሪ እንጂ ወራሪ ተፈናቃይ እንጂ አፈናቃይ አይደለነም ፤

✔️አማራዊ ማንነታችን የወሰን አስተዳደር ግዛት በህግ አግባብ ይከበር!
✔️ወልቃይት ጠገዴ የከለዉ ልጅ የአማራ ዘር ግንድ መነሻ ነዉ!!

(ዳንሻ ከተማ ኮሙኒኬሽን)

ይህ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ በአደባባይ ያሰማው ድምፅ ነው!

“አማራ ነን አልን እንጅ አማራ እንሁን ብለን አልጠየቅንም” ብሏል ህዝብ በነቂስ ወጥቶ።

ወንጀለኞች ለህግ ይቀርባሉ እንጅ በተፈናቃይ መልክ እናስፍር አይባልም!

ከትግራይ ጋር ደንበራችን ተከዜ ነው። ነፃ ወጥተናል። በህግ ይረጋገጥ።

ብሏል የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ።ለትህነግ የሚሰሩ የውጭ የሰብአዊ ድርጅቶችን የቅጥፈት ሪፖርት አውግዟል።

ከትግራይ ህዝብ ጋር መልካም ጎረቤት ሆነን ለመቀጠል ችግር የለብንም ብሏል ህዝብ በአደባባይ።

መሪዎቻችንና ህዝብ ላይ የሚደረግን ስም ማጥፋት ወደበለጠ ትግል ያመራናል ብሏል።